ጤንነትና ደህንነት በስራ ቦታ

This page was last updated on: 2023-05-06

የአሰሪ ክብካቤዎች

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት ማንኛውም አሠሪ የሠራተኞች ደህንነትና ጤንነት በሚገባ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡

ሠራተኛ ለሥራ ምቹ በሆነ የሥራ አካባቢ ደህንነቱና ጤንነቱ በሚገባ ተጠብቶ የመሥራት መብት አለው፡፡ አሠሪ ሠራተኛን በህይወቱ ላይ አደጋ ሊደርስበት በሚችል አኳኋን እንዲሠራ ማድረግ ህገ-ወጥ ድርጊት ነው፡፡

ሰራተኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችል ስጋት እና ከባድ አደጋ እና በጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን በመከላከል አስፈላጊ የሆኑ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ በአግባቡ እንዲያውቁ መደረጋቸውን ለማረጋገጥ አሰሪው አግባብነት ያለውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ አዲስ የተቀጠሩ ሰራተኞች እና አደገኛ በሆኑ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን የጤና ምርመራ በአሰሪው ወጪ ማካሄድ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁሉም የስራ ሂደቶች ለሰራተኞች ደህንነት እና ጤንነት አካላዊ፣ ኬሚካላዊ፣ ባይሎጂካዊ፣ ኤርጎኖሚካዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የሚያደርሱ ምንጭ መሆን የለባቸውም፡፡

አሰሪው በድርጅቱ ውስጥ በሚኒስቴሩ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት የስራ ደህንነት እና ጤንነት ኮሚቴ ማቋቋም የአሰሪው ግዴታ ነው፡፡ የስራ አደጋዎች እና የስራ በሽታዎች መመዝገብ እና ለስራ ተቆጣጣሪ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የስራ አካባቢን ከሰራተኞች ደህንነት እና ጤና ላይ ጎጂ ከሆኑ አደጋዎች ነጻ ለማድረግ አሰሪው በዚህ አዋጅ መሰረት አግባብነት ካለው ባለስልጣን በሚሰጠው መመሪያ መሰረት መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ሰራተኞችም በአሰሪው ወይም አግባብነት ባለው ባለስልጣን የሚሰጡት የደህንነት እና የጤንነት ጥንቃቄ መመሪያዎችን ሁሉ ማክበር እና የራሱን ደህንነት እና ጤና ለመጠበቅ የሚወጡ መመሪያዎችን በማዘጋጀት እና በመፈጸም መተባበር ይኖርባቸዋል፡፡

ሰራተኞች ለደኅንነት ሲባል የተቀመጡ የደኅንነት መጠበቂያ ዕቃዎችን ወይም ሌሎች መሣሪያዎችን መነካካት፣ ማንሳት፣ ያለ ቦታቸው ማስቀመጥ፣ማበላሸት ወይም ማጥፋት የለባቸውም፡፡ እንዲሁም ሰራተኞች ሥራ ላይ የሚደርስ አደጋን ለመቀነስ ሲባል የሚሰራበትን ማንኛውንም ዘዴ ወይም አሠራር ማሰናከል የለባቸውም፡፡

ምንጭ፡-የተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀፅ 14(1ሠ) እና ከአንቀፅ 92-93

ነፃ መከላከያ

የስራ ህጉ አሰሪዎች ለሰራተኞች የአደጋ መከላከያ መሣሪያ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶች በማቅረብ ሰራተኞች ላይ ሊደርስ የሚችል የአደጋ እና የሌሎች በሠራተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግር ስጋቶችን ማስወገድ ይጠበቅበታል፡፡

 

ምንጭ፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 92(3)

ስልጠና

አሰሪው ሰራተኞች የሚሰሩት ስራ ሊያስከትልባቸው ስለሚችለው አደጋ እንዲሁም በጤንነት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለማስወገድ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄ ተገቢውን ስልጠና እንዲሰጥ ይጠበቅበታል፡፡ አሰሪው በተጨማሪ ለሰራተኞቹ የመከላከያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ስለመጠቀም መመሪያ መስጠት ይኖርበታል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 92(2)

የስራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎት

.- የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ጉልህ የሆነ የስራ ቁጥጥር  አገልግሎትን ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን አሁን በሥራ ላይ ያለው ሥርዓት ከዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ስምምነት 081 ጋር የተጣጣመ አይደለም፡፡ በሀገሪቱ 380 የሚጠጉ የሥራ መርማሪዎች አሉ ነገር ግን በአቅርቦቶች እጥረት ምክንያት መርማሪዎቹ ደረጃዎችን በብቃት ለማስተባበር አይችሉም፡፡

የስራና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ደህንነት፣ ጤንነት እና የስራ አካባቢ ዲፓርትመንት የስራ ቁጥጥር የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/2003 የሰራተኞች አገልግሎት፣ የስራ ሁኔታዎች፣ የሰራተኞች ጤንነት እና ደህንነት፣ በአጠቃላይ የስራ ህጎች ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለማጥናት እና ለመመርመር የሚችል የሶስትዮሽ የስራ አማካሪ ቦርድ የመመስረትን አስፈላጊነት ይደነግጋል፡፡ የስራ ተቆጣጣሪዎች የቁጥጥር አገልግሎትን ለመከታተል እና ሱፐርቫይዝ ኃላፊነት ለመወጣት በሚኒስቴሩ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ብሔራዊ ድንጋጌ በስራ ሰዓት ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ወደ ጊቢ የመግባት እና እርምጃዎችን የመውሰድ፣ ፎቶግራፍ የማንሳት፣ ናሙና የመውሰድ እና ለምርመራ እና ለፈተና የሚረዳቸውን መዛግብት የመውሰድ፣ የመመርመር የመዝገቦችን ኮፒ ወይም ከመዝገቦች የተወሰዱትን ሰነዶች፣ የምስክር ወረቀቶች፣ ማስታወቂያዎች የመውሰድ እና ማንኛውንም ሰው ቃለ መጠይቅ የማድረግ እና አግባብነት ባለው የስራ ቦታ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ማስታወቂያዎች መለጠፋቸውን የማረጋገጥ ስልጣን ለስራ ተቆጣጣሪዎች ይሰጣል፡፡

 

የስራ ተቆጣጣሪ አሰሪዎችን እና ሰራተኞችን የህግ ድንጋጌዎችን ለማሟላት እና በሰራተኞች ጤና፣ ደህንነት እና መልካም ህይወት ላይ አጠቃላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ለማስወገድ እጅግ ተመራጭ ዘዴዎች ላይ ወይም በሰራተኞች ጤንነት እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንዳይደርስ ለማድረግ የሚያስፈልጉ እርምጃዎች ላይ አሰሪዎችን እና ሰራተኞችን ምክር ይሰጣሉ፡፡ አንድ ተቆጣጣሪ በስራው አማካኝነት ያገኘውን ማንኛውንም መረጃ ይፋ አለማድረግ እና በስራ ግጭት ውስጥ በህብረት ስምምነት ውስጥ እንደ አስታራቂ ወይም አደራዳሪ ሆኖ ከመሳተፍ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

አሰሪው ወይም ተወካዩ በተጨማሪም ለተቆጣጣሪው ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና ስራውን በሚሰራበት ጊዜ ጣልቃ አለመግባት አለበት፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 177-182

ጤንነትና ደህንነትን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ ቁ. 377/2003 / Labour Proclamation No.377/2003
loading...
Loading...